Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሥምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

ተቋማቱ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች ፍላጎት የተቃኘ ትምህርትና ሥልጠና ለመስጠት፣ በዕውቀት፣ በክኅሎት፣ በአመለካከት እና በሙያዊ ሥነ-ምግባር ብቁ የሆኑ ሙያተኞችን ለመፍጠር፣ ለሀገር ዕድገት እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በሚረዳ መልኩ በቴክኖሎጂና በምርምር ሥራዎች ላይ በጋራ ለመሥራት ነው የመግባቢያ ሥምምነቱን የተፈራረሙት፡፡

ስምምነቱን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ሙክታር ሙሀመድ ናቸው።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ዕድገት በጋራ ይሠራሉ ፣ በዩኒቨርሲቲው የሚከናወኑ ማኅበረሰብ ተኮር ጉዳዮችንም በሚዲያ ተደራሽ ለማድረግ ይተባበራሉ ተብሏል፡፡

በመራዖል ከድር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.