Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሩሲያ የአፍሪካ አጋርነት ፎረም ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሩሲያ አፍሪካ አጋርነት ፎረም ሃላፊ አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

በውይይቱ አምባሳደር ኦዜሮቭ  በመጭው ሀምሌ ወር በሩሲያ ሴንት ፒተርበርግ ስለሚካሄደው ሁለተኛው የሩሲያ – አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዝግጅት ገለጻ አድርገዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ላላት ታሪካዊ ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለሩሲያው ልዑክ ማብራሪያ መስጠታቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.