Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ የርዕደ-መሬቱ አደጋ ከደረሰ 10 ቀናት በኋላ ሰዎች በሕይወት እየተገኙ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ እና ሶሪያ የርዕደ-መሬት አደጋ ከተከሰተ 10 ቀናት በኋላ ሰዎች በሕይወት እየተገኙ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

እንደ ዌስት ሜዝ ዘገባ የነፍሥ አድን ሠራተኞች በርዕደ-መሬቱ የአቧራ ብናኝ የተሸፈኑትን ከተሞች ሲያፀዱ ነው በሕይወት የተረፉት አንድ ሕፃን ልጅ ፣ አንድ ሴት እና ሁለት ወንዶች በህይወት የተገኙት።

እስካሁን በሁለቱ ሀገራት በተከሰተው ርዕደ መሬት 44 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

በቱርክ የ38 ሺህ 44 እንዲሁም በሶሪያ ደግሞ የ5 ሺህ 800 ሰዎች ሕይወት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ማለፉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.