Fana: At a Speed of Life!

የሲሚንቶ፣ የብረትና የድንጋይ ከሰል አምራቾች ሀገር በምትፈልገው ልክ ማምረት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲሚንቶ፣በብረትና የድንጋይ ከሰል ምርት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ሀገር በምትፈልገው ልክ መስራት እንደሚጠበቅባቸው የማዕድን ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ ከሲሚንቶ ፣ ከብረትና ከድንጋይ ከሰል አምራች ኩባንያዎች ጋር በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ከማእድን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይታቸውም ዘርፉ ለሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መሳካት ወሳኝ በመሆኑ በቅንጅት በመስራት ውጤት ማምጣት አለበት ብለዋል፡፡

መንግስትም የሚጠበቅበትን ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.