Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቱርክ እና ሶሪያ የሰብዓዊ እርዳታ የማጓጓዝ ሒደትን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቱርክ እና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማዳረስ የሚደረገው ጥረት ተቀላቀለ፡፡

በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውፕላኖች ከሜክሲኮ በአደጋው ተጎጂ ለሆኑ ቱርካውያን የተደረገውን 100 ቶን የሰብዓዊ እርዳታ እያጓጓዙ መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቱርክ እና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስካሁን ከ41 ሺህ በላይ ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ በርካቶች ደግም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.