Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከቱርኩ ዲ ኢ ሲ ግሩፕ ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከታዋቂው የቱርክ ደርጅት ዲ ኢ ሲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል እና የዲ ኢ ሲ ምክትል የቦርድ ሊቀመንበር አቲ ሀቢል ያዚጀ ተፈራርመውታል፡፡

ስምምነቱ የቱርክና የኢትጵያን ግንኙነት ከማጠናከር አኳያ የራሱ አሻራ የሚኖረው ሲሆን፥ የፌዴራል ቤቶቸ ኮርፖሬሽንን በቴክኖሎጂ እና በእውቀት ሽግግር ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በአቅም ግንባታ እና ሌሎች የቤት ልማት ዘርፉን ሊያሳድጉ የሚችሉ ድጋፎችን ኮርፖሬሽኑ ማግኘት የሚያስችለው ስምምነት እንደሆነም ነው የተነገረው፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል÷ በሁለቱ አካላት የተፈጸመው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል በዘለቀው ታሪካዊ ወዳጅነትና ትብብር ላይ የራሱ አሻራ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽኑ በትብብር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠው ከኮርፖሬሽኑ ጋር በትብብር አብሮ ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነትና ፍላጎት፣ ለዲ ኢ ሲ ግሩፕ እና አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አቲ ሀቢል ያዚጀ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ሌሎች ሥራዎችን የማከናወን እቅድ እንዳላቸው ጠቁመው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በትብበር በመስራት ለቤት ልማት ዘርፉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የጀመረውን የቤት ልማት ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን አዋጭና ወጪ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚያቀርቡም ነው የተናገሩት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.