Fana: At a Speed of Life!

በአውስትራሊያው የዓለም ሀገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያውያን ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ እየተካሄደ በሚገኘው 44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

አስቀድሞ በተከናወነው በ8 ኪሎ ሜትር ድብልቅ ሪሌ ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ከ20 ዓመት በታች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ሰናይት ጌታቸው 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ሲሆን÷ መዲና ኢሳ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

በ8 ኪሎ ሜትር ከ20 ዓመት በታች የወንዶች ውድድርም እንዲሁ የነሐስ ሜዳሊያ በቡድን መመዝገቡን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.