Fana: At a Speed of Life!

ኮሞሮስ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርነትን ከሴኔጋል ተረከበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሞሮስ የ2023 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን ከሴኔጋል በይፋ ተረክባለች።

36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።

በጉባዔው መክፈቻ መርሐግብር የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ መንበር ሴኔጋል ለኮሞሮስ ሊቀ መንበርነቷን በይፋ አስረክባለች።

የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በ2023 የአፍሪካ ሕብረትን በሊቀ መንበርነት ይመራሉ።

የ2022 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የነበሩት የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.