Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ እና በሶሪያ ርዕደ-መሬት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 45 ሺህን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ እና ሶሪያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 45 ሺህን መሻገሩ ተገለጸ፡፡

ጋናዊው እግር ኳስ ተጫዋች ክርስቲያን አትሱም በቱርኩ ርዕደ-መሬት ሕይወቱ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ክርስቲያን አትሱ አንድ የውድድር ዘመን ለሳዑዲ ዓረቢያው አል-ራኢድ ከተጫወተ በኋላ÷ ባለፈው መስከረም ወር ወደ ቱርክ አቅንቶ ለቱርኩ ሃታይስፖር መፈረሙ ይታወሳል፡፡

የ31 ዓመቱ ክርስቲያን አትሱ ለኒውካስል ዩናይትድ፣ ቸልሲ፣ ኤቨርተን እና ቦርንማውዝ ክለቦች መጫወቱ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል አደጋው ከደረሰ ከ11 ቀናት በኋላ አንድ የ45 ዓመት ሰው በሕይወት መገኘቱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

እስካሁን በቱርክ 39 ሺህ 672 እንዲሁም በሶሪያ ከ5 ሺህ 800 በላይ ሰዎች በርዕደ-መሬት አደጋው ሕይወታቸው አልፏል፡፡

በአደጋው ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ለተለያዩ 1 ሺህ 589 ሕፃናት የቱርክ መንግስት ድጋፍ እያቀረበ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.