Fana: At a Speed of Life!

ጉድለትን ለይቶ በመፍታት ውጤት ለማስመዝገብ መስራት ይገባል- አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግማሽ ዓመቱ የታዩ ጉድለቶችን ለይተን በመፍታት ለውጦችን አስቀጥለን ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት አለብን ሲሉ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

የሲዳማ ክልል አስፈፃሚ አካላት ተቋማት የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በመስተዳድር ምክር ቤት ደረጃ እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት÷ በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት እንደ ክልል በሁሉም ዘርፍ ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በተሠሩ ሥራዎች ጥሩ ውጤት የታየበት ስለሆነ ለአርሶአደሩ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የቡና ምርት በሚፈለገው ደረጃ እየሄደ ስለመሆኑ ጠቁመው የተፋሰስ ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም በእንስሳት እርባታ፣ በሌማት ትሩፋት ስራዎች የቤተሰብን ብልጽግና ለማረጋገጥ ትኩረት መሰጠቱን ነው የጠቆሙት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.