Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አወል አርባ የተመራ ልዑክ በአሚበራ ወረዳ የለማ የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜትን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቶ አወል አርባ የተመራ ልዑክ የወረር ግብርና ማዕከል ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር በአሚበራ ወረዳ በ 110 ሄክታር መሬት ላይ ያለማውን የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት ጎበኘ።

የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት ሥራው በአሚበራ ክላስተር ከለማው በተጨማሪ በዱብቲ ወረዳ እየለማ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በስፋት ምርጥ ዘሩን ማባዛት ያስፈለገው በቀጣይ የምርት ዘመን እጥረት እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷ ክልሉ በምግብ ራስን መቻል ቀዳሚ አጀንዳው በማድረግ ከምርጥ ዘር አቅርቦት ጀምሮ ለቅድመ ምርት፣ ምርት እና ድኅረ ምርት ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶ እየሠራ ነው፡፡

ለዚህም ድጋፍና ክትትል በማድረግ ውጤታማ ሥራ መከናወኑን ነው የተናገሩት፡፡

የተገኘው አበረታች ውጤት ለተሻለ ሥራ እና ትጋት የሚያነሳሳን በመሆኑ ለቀጣይ ሥራዎች ታጥቀን መነሳት አለብን ብለዋል፡፡

ልዑኩ ከምርጥ ዘር ብዜት ሥራው በተጨማሪ በምርት ዘመኑ በአሚበራ በ1 ሺህ 821 ሄክታር ላይ በክላስተር የለማውን የስንዴ ምርት ጎብኝቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.