Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ላይ ለችግር ለተጋለጡ ሰዎች የሚውል የ250 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም አገራት በችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ለመርዳት የሚውል 250 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል፡፡

ድጋፉ የተለቀቀው በመንግሥታቱ ድርጅት ማዕከላዊ የእርዳታ ምላሽ ፈንድ አማካኝነት ነው፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከ339 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለችግር ተጋልጠዋ ብለዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ ብልጫ አለው ማለታቸውን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዜጎቹ በተደጋጋሚ በሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥ፣ በኢኮኖሚና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት ለማኅበራዊ ቀውስ መጋለጣቸውን ዋና ጸሐፊው ጠቁመዋል።

የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትም የምግብ ዋጋ እንዲያሻቅብና በርካታ ዜጎች ለርሃብ እንዲጋለጡ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

ይህም የተቋሙን ሥራ በእጅጉ አወሳስቦታል ነው ያሉት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፡፡

የዓለም የፋይናንስ ተቋማት÷ ሀገራት ችግር ሲጋረጥባቸው ለማገዝ የሚያስችላቸውን አሠራር መዘርጋት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

በተለይም ዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ማድረግ አለባቸው ተብሏል በመግለጫው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.