Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ይደነቃል- ፋኦ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትየሚደነቅ መሆኑን የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዳይሬክተር ጀነራል ቹ ዶንግዩ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና ላይ እየሰራች ያለችው ስራም ትልቅ ለውጥ የተመዘገበበት መሆኑን ነው ዳይሬክተር ጀኔራሉ የገለጹት፡፡

የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዳይሬክተር ጀነራል ቹ ዶንግዩ እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን እየተከናወነ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በሉሜ ወረዳ ቆቃ አካባቢ በ5 ሺህ ሄክታር ላይ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝ የበጋ መስኖ ስንዴን ተመልክተዋል።

ፋኦም ይህንን ስራ በቴክኖሎጂና ሙያዊ እገዛ በመስጠት ድጋፍ እንደሚያ ደርግ ዳይሬክተር ጀነራሉ አረጋግጠዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ÷ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የውሃ ሃብቷን መጠቀም በመጀመሯ፣ የውሃ ፓምፕ በመንግስት ድጋፍ መቅረቡና የእርሻ ማሽነሪዎችንም ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በመደረጉ በስንዴ ምርት ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ፋኦ የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ በምርጥ ዘርና በተለያየ ቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደሚያደርግ መስማማታቸውንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.