Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ መሪዎች የወባ መከላከል ጥምረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ7 ሀገራት ዕውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ መሪዎች የወባ መከላከል ጥምረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሩዋንዳ፣ ጋና፣ ዛምቢያ፣ ታንዛኒያ እና ኬንያ በወባ በሽታ መከላከል ላይ ባከናወኑት ተግባር እውቅና ሰጠ፡፡

የአፍሪካ መሪዎች የወባ መከላከል ጥምረት ሽልማት መርሐ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።

የጥምረቱ ሊቀመንበር የጊኒቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ እንደገለጹት÷ የአፍሪካ ሕብረት በ2030 የወባ በሽታን ለመቀነስ ያስቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

በዓለም በወባ በሽታ ሕይወታቸው ከሚያልፈው 98 በመቶው በአፍሪካ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመሆኑም በሽታውን ለመከላከል ተጨማሪ የ15 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የሚያስፈልግ በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትብብር እንዲያደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.