ነጻና የታፈረች ሀገር የሰጡንን ሰማዕታት የምናስባቸው አንድነትን ከሚንዱ አስተሳሰቦች በመራቅ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን የምንኮራባት፣ ነጻና የታፈረች ሀገር የሰጡንን ሰማዕታት የምናስባቸው ከሚከፋፍሉና አንድነትን ከሚንዱ አስተሳሰቦች በመራቅ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
ከንቲባዋ ፥ የ86ኛዉን የካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ሀዉልት ተገኝተው የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ችግሮች ሲያጋጥሙ በመወያየት ፣ በመመካከርና ሌት ተቀን በመስራት ከድህነት መላቀቅ ይገባልም ነው ያሉት፡፡