Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ዓለምአቀፋዊ ትብብርን በማጎልበት ረገድ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ነው – ቭላድሚር ፑቲን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ባለ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሰብዓዊ ትብብርን በማጎልበት ረገድ አይነተኛ ሚና  እየተጫወተ እንደሚገኝ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን 36ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን አስመልክተው ለተሳታፊዎች የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው÷የአፍሪካ ሀገራት  ለሩሲያ የምንጊዜም አጋር መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በፈረንጆቹ 2019 የተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በአገራቸውና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሁለትዮሽና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነት ማጠናከር ያስቻለ መሰረት መጣሉንም ገልጸዋል።

“በመጪው ሐምሌ በሩሲያ ፒተርስበርግ ከተማ የሚካሄደው ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በቀጣይ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ፍሬያማ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ምክክር መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት መገለፃቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.