Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በጋራ እየሰሩ ነው- የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሶማሊያ በቀጣናው የሚታየውን ሽብርተኝነት ለመዋጋት በጋራ እየሰሩ መሆኑን የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብሽር ኦማር ሁሩሲ ገለጹ።

በ36ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፋ የሚገኙት የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብሽሬ ኦማር÷ሁለቱ ሀገራት በዘርፈ ብዙ የትብብር መስኮች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራቱ  የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት እንዲሁም በርካታ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶች የሚጋሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በፖለቲካ፣ በምጣኔ ሃብታዊና ማህበራዊ መስኮች ጭምር የተጠናከረ ግንኙነት ያለቸው መሆኑን ጠቅሰው የትብብር ግንኙነቱ ቀጣይነት እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ የሽብር ቡድኖችን ለመዋጋትና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ጥረት ስታደርግ መቆየቷን ያስታወሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ  ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በጋራ እየሰሩ መሆኑንም አመላክተዋል።

የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀጣይም ሁለቱ አገሮች የትብብር ግንኙነታቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.