Fana: At a Speed of Life!

36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

እንግዶቹ ወደ አዲስ አበባ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት የፀጥታና ደኅንነት ችግር ሳይገጥማቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የፀጥታ ተግባር ማከናወን መቻሉን ግብረ ኃይሉ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተለመደውን የእንግዳ ተቀባይነት ባህል በማሳየት የፀጥታ ኃይሉ የሚሰጠውን መመሪያ በመቀበል አጋርነታቸውን በማሳየት የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ እንዲረጋገጥ እገዛ በማድረጋቸው ግብረ ኃይሉ አመስግኗል፡፡

እንዲሁም በጥብቅ ሥነ ምግባር እየተመሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በስኬት ለተወጡ ለፀጥታና ደህንነት አመራሮችና አባላት የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.