Fana: At a Speed of Life!

በ16 ሚሊየን ብር የተገነባው የደጀን በር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ በ16 ሚሊየን ብር የተገነባው የደጀን በር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ፡፡

ትምህርት ቤቱ 10 መማሪያ ክፍሎች፣ አንድ አ ይሲ ቲ ክፍል እና ስምንት መፀዳጃ ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን÷ ግንባታው በአራት ወራት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ይህ ቅድመ መደበኛና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክልል ደረጃ ለሚከናወነው የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሳደግ ሥራ አዎንታዊ አስተዋጽዖው የጎላ ነው ተብሏል፡፡

የግንባታው ወጪ በዳሸን ባንክ መሸፈኑንየአማራ ልማት ማኅበር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዓለማየሁ ሞገስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በኤልያስ አንሙት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.