Fana: At a Speed of Life!

ፆምና የጤና ጠቀሜታው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፆም ሀይማኖታዊ ሥርአትን ተከትሎ የሚከወን ተግባር ነው።

ለተወሰነ ሰዓት ከምግብና ከመጠጥ መራቅ ወይም መጾም ደግሞ ከሀይማኖታዊ ጥቅሙ በዘለለ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ጥናቶች ያመለክታሉ።

ከዋና ዋና ጠቀሜታዎቹ መካከል በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር፦ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጾም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠርና በተለይም የስኳር በሽታ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ መሆኑ ነው የተጠቆመው።

እብጠትን መከላከል፦ ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጡ ጥናቶች በጾም ወቅት ሰውነት የሚያገኘው የካሎሪ መጠን ስለሚቀንስ ሰውነት ላይ የሚከሰት እብጠትን ለመቀነስ ይረዳል።

የደም ግፊትን እና የኮሌስትሮል መጠንን ለመከላከልና ክብደት ለመቀነስም ያግዛል።

የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ፦ በዚህ ረገድ የደም ግፊትና የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ ይረዳል።

ይህ ደግሞ ከልክ በላይ በሆነ ውፍረት ሊከሰት የሚችለውን የልብ ጤንነት ችግር መቅረፍ ያስችላልም ነው የተባለው።

ፆም የአዕምሮ የመስራት አቅምን ያፋጥናል፣ ከነርቭ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ይከላከላል፣ የካንሰር ተጋላጭነትን ለመከላከል እና ለምግብ መፈጨትና ለስርአት ምግብ መንሸራሸርም ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ለአጥንት ጥንካሬ ወሳኝ የሆነውን ሆርሞን እድገት ለመጨመር እንደሚረዳም ነው የተጠቆመው።

ለልብ ጤንነት፣ አዕምሮ በአግባቡ ስራውን እንዲከውን ለማድረግ፣ የምግብ መፈጨት ስርዓትን ለማስተካከል፣ የጠራ የሰውነት ቆዳ እንዲኖር ለማድረግ እንደሚረዳም የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ ያደረገው የዌብ ሜድ እና ኸልዝ ላይን ዘገባ ያመላክታል።

በሽታ የመከላ ከል አቅምን ይጨምራል፦ መጾም ሰውነት በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲጨምር ይረዳል።
ይህም በሽታ አምጪ ነገሮችን እንዲሁም ካንሰር አምጬ ሴሎች እንዳያድጉ ያደርጋል።

የአዕምሮን የማሰብ አቅም ይጨምራል፦ ጾም አዕምሮ “ብሬይን ድራይቭድ ኒውሮትሮፊክ ፋክተር” የሚባል ፕሮቲን እንዲያመርት ይረዳዋል።

ይህም አእምሮ ጤነኛ እንዲሆን የሚያደርገው ሲሆን ፕሮቲኑ ከዕእምሮ ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ መዘንጋት ያሉ በሽታዎችን ይከላከላል።

እርጅናን ሊያዘገይ እና ረጅም እድሜ ሊጨምር እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጾም ከጤና ጠቀሜታ ባለፈ የድብርትና ጭንቀት ስሜትን ለማስወገድ እንደሚረዳም ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.