Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ የሚሳኤል ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡

ፒዮንግያንግ በምስራቅ የባህር ዳርቻ የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የደቡብ ኮሪያ ጦርም ሁለቱን የሚሳኤል ሙከራዎች በጽኑ አውግዟቸዋል።

ሚሳኤሎቹ ዛሬ ማለዳ ላይ ከሰሜን ኮሪያ ዋና ከተማ በስተሰሜን ከምትገኝ ከምዕራባዊ የባህር ዳርቻ ከተማ መወንጨፋቸውን የደቡብ ኮሪያ የጦር ሃላፊዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የሰሜን ኮሪያ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያም ሚሳኤሎቹ እንደቅደም ተከተላቸው 395 እና 337 ኪሎ ሜትር ርቀት ኢላማዎችን ለመምታት የሚያስችሉ ናቸው ብሏል።

ዛሬ ማለዳ ላይ የተወነጨፉት ሚሳኤሎች አንዱ 400 ኪሎ ሜትር ሌላኛው ደግሞ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ከተወነጨፉ በኋላ መውደቃቸውን የአል ጀዚራ ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.