Fana: At a Speed of Life!

የአጎዋን ዕድል ለማስመለስ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአጎዋን ዕድል ለማስመለስ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ባለሙያ የሆኑት አቶ ሐብቱ ማሞ ገለጹ፡፡

አሜሪካ በኢኮኖሚ ለመደገፍ የቀረጸችው ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ ወደሀገሪቱ የማስገባት የንግድ ዕድልን (አጎዋ) ኢትዮጵያ በሰሜኑ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ እንዳጣች የሚታወስ ነው፡፡

በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ባለሙያ የሆኑት አቶ ሐብቱ ማሞ ፥ የአጎንዋ ዕድል ለማስመለስ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከአጎዋ ጋር በተያያዘ የገበያ ዕድላቸው የተዘጋ ኩባንያዎች ዘግተው እንዳይሄዱ አማራጭ የገበያ መዳረሻ እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

ይህም ሆኖ ምርት ያቆሙ ኩባንያዎች እንዳሉ ጠቅሰው ፥ አምራቾቹ የሀገር ውስጥ ገበያን እንደአማራጭ ተጠቅመው ምርታቸውን ማምረት እንዳልቻሉም አንስተዋል።

በዚህም የአጎዋን እድል ለመመለስ ከመንግስት፣ ከአሜሪካ የተለያዩ ሲቪል ምክር ቤቶችና ሌሎች አካላት የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉም ነው ባለሙያው የተናገሩት፡፡

የፌዴራል መንግስትና ህወሓት ካደረጉት የሰላም ስምምነት በኋላ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት እየታየ ሲሆን ፥ አጎዋ ዳግም የሚጀመር ከሆነ ፍሰቱ ይበልጥ እንደሚጨምርም ነው የሚናገሩት።

የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ረጋሳ በበኩላቸው ፥ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ብዙ ባለሀብቶች ያለውን ሁኔታ በመመልከት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የቦሌ ለሚ ኢንዱስሪ ፓርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ትንሳዔ ይማም ፥ ባለሃብቶች ውጤታማ የሆነ ምርት የሚያመርቱበት ሁኔታዎች እንዲዲያመርቱ እንዲመመቻችላቸው ከማድረግ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ድጋፎችና እገዛዎች ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አብዛኛውን ምርቶች በሀገር ውስጥ ለማምረት ጥረት እያደረገች ሲሆን ፥ በዚህም ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ከፍተኛ ትኩረት እያደረገና ዕድሎቹን እያመቻቸቸ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ላይ እንዲሳተፉ ኮርፖሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፥ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ኢንቨስትመንቱ መቀዛቀዝ አሳይቶ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እየመጡ መሆኑን ነው ያነሱት፡፡

የሚታዩ አማራጮችን ታሳቢ ያደረገ የአንድ ዓመት ቀጥተኛ የውጭ የኢንቨስትመንት ፍሰት 6 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቅሰዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.