Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሱዳን የሉዐላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተና ጀነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን ጋር በስልክ ተወያዩ።

በነበራቸው ቆይታም ለኮቪድ19 ቀውስ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በቅርበት ስለ መሥራት ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በዚህ ፈታኝ ወቅት የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስር ስለ ማጠናከር እና በሱዳን ላይ የተጣለውን ማዕቀብ የማስነሳትን ሥራ ስለ መከወን ዙሪያ መምከራቸውንም ገልፀዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.