Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ቻይና የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ የሚያስችል ቡድን ለማቋቋም ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ቻይና የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ የሚያስችል ቡድን ለማቋቋም የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ መግባቸው የሚታወስ ሲሆን ፥ በሀገራቱ የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በዚሁ መድረክ ኢትዮጵያ እና ቻይና የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነትን፣ ኢንቨስትመንትንና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ የሚያስችል ቡድን ለማቋቋም ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የቻይና የንግድ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር ሊ ፌይ ተፈራርመዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.