Fana: At a Speed of Life!

ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2015/16 የሰብል ዘመን ከውጭ ከሚገባው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 3 ሚሊየን 460 ሺህ 526 ኩንታል ማዳበሪያ ለዩኒየኖች እየተሠራጨ መሆኑን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገለፀ።

ኮርፖሬሽኑ ለ2015/16 የሰብል ዘመን 12 ሚሊየን 875 ሺህ 520 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እየሠራ ነው።

ከዚህ ውስጥ 7 ሚሊየን 875 ሺህ 520 ኩንታሉ ኤን ፒ ኤስ እና ኤን ፒ ኤስ ቦሮን መሆኑን በኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ጋሻው አይችሉህም ተናግረዋል።

5 ሚሊየን ኩንታሉ ደግሞ ዩሪያ ማዳበሪያ ነው ብለዋል፡፡

እስከ ትናንት ድረስም 3 ሚሊየን 480 ሺህ 860 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ መድረሱንን ነው አቶ ጋሻው የተናገሩት።

እንዲሁም 500 ሺህ ኩንታል ዩሪያ የጫነች መርከብ ነገ ጂቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.