Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋር ቡድን አባላት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋር ቡድን አባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

ውይይቱን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ናቸው።

በውይይቱ በኢትዮጵያ ስለደረሰው ጉዳት እና የፍላጎት ግምገማ ላይ ለአጋሮቹ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ፥ የኢትዮጵያን የማይበገር የማገገምና የመልሶ ግንባታ እቅድ ማዕቀፍ ዳሰሳ ወደ ተግባር ማሸጋገርንና መሰል ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የኤጀንሲዎች ኃላፊዎች እና ልዑካኑ የኢትዮጵያን የማገገም እና የመልሶ ግንባታ እቅድን ማድነቃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የማገገሚያ ወይም የመልሶ ግንባታን አስፈላጊነት ያነሱት ልዕካኑ ለተግባራዊነቱ የለጋሾች ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.