Fana: At a Speed of Life!

ትኩረቱን ፓን አፍሪካኒዝም ላይ ያደረገ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ትብብር የተዘጋጀና ፓን አፍሪካኒዝም ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወጣት ቢሆንም የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የፓን አፍሪካኒዝም ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የፅሁፍ ስራዎች መታተማቸውን አስረድተዋል።

በመድረኩ ላይ እውቁ ፕሮፌሰር ሀኪም አሊ “የአፍሪካ ዳያስፖራ እና የአፍሪካ እድገት” በሚል ርእስ ፅሁፍ አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር ሀኪም በፅሁፋቸው ላይ የፓን አፍሪካኒዝምን ምንነት እና ታሪክ አንስተዋል።

በተጨማሪም አፍሪካውያን ዳያስፖራዎች ለአህጉሪቱ እድገት የሚኖራቸው ሚና የሚናቅ ባለመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

መሰል መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።

በፍቅርተ ከበደ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.