Fana: At a Speed of Life!

3 የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላት እስከ 1 ዓመት ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተሠራ ነው- ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር፣ ሐዋሳ እና መቀሌ የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላት ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ እየተሠራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

በሚኒስቴሩ የካንሰር መቆጣጠር አማካሪ ዶክተር ኩኑዝ አብደላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ አሁን ላይ በሦስት ማዕከላት የካንሰር ህክምና እየተሰጠ ነው።

ተጨማሪ ሦስት ማዕከላትን በቀጣይ ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተጨማሪ የጅማ እና የሃረማያ የካንሰር ህክምና ማዕከላት ወደ ስራ መግባት በተወሰነ መልኩ ጫናውን ቀንሷል ነው ያሉት ዶከተር ኩኑዝ።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የካንሰር ህክምና ማዕከል የካንሰር ክፍል ኃላፊ ዶክተር አማረ አሰፋ እንደገለጹት÷ የጅማ ማዕከል በቀን እስከ 110 የሚሆኑ ታካሚዎችን እያስተናገደ ነው።

ማዕከሉ በቀን የማስተናገድ አቅሙን ከ250 በላይ ለማድረስ ተጨማሪ ማሽን እያስገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.