Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ116 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታና ማስፋፊያ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ116 ሚሊየን 300 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ በተለያዩ ከተሞች የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታና ማስፋፊያ ሥራ እያከናወነ ነው፡፡

የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ የሚከናወነው÷ ከከሚሴ እስከ ቦሩ ሃረዋ፣ ከመሃልሜዳ እስከ ዘመሮ፣ ከባህር ዳር እስከ አዴት፣ ከሊብሶ ጎራርባ ወረቃሉ እስከ ውርጌሳ፣ ከሐሮ እስከ ድሬሮቃ እና ከቢቸና ሰብስቴሽን እስከ የዕድ ውሃ ባሉ አካባቢዎች በተዘረጉ መስመሮች ላይ ነው፡፡

እንዲሁም የመካከለኛ መስመር ማስፋፊያው÷ ከኮምቦልቻ ሰብስቴሽን እስከ ካርቪኮ፣ ከሞጆ ሰብስቴሽን-እጀሬ፣ ከእጀሬ እስከ አረርቲ፣ ከጣና በለስ ሰብስቴሽን እስከ ቁንዝላ ባሉ ቦታዎች ላይ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ በሦስተኛ ወገን አማካኝነት እየተከናወነ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅት 149 ነጥብ 95 በኪሎ ሜትር መዘርጋት ተችሏል መባሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታና ማስፋፊያ ስራ መከናወኑ በከተሞቹ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝና ቀልጣፋ ያደርገዋል ነው የተባለው፡፡

የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት ኑሮና የከተሞቹን እድገት ለማሻሻልም እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡

ለኢንዱስትሪ፣ ለውሃ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት መስፋፋት አይነተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታልም ነው የተባለው።

ባለፉት ስድስት ወራት የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ 72 ነጥብ 45 በመቶ እንዲሁም የማስፋፊያ ስራው 86 ነጥብ 28 በመቶ ተጠናቋል፡፡

ፕሮጀክቱን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.