Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ በሚጣለው አዲስ ማዕቀብ  ስምምነት ላይ አለመድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ባቀረቡት ሃሳብ ላይ አለመስማማታቸው ተገልጿል፡፡

ህብረቱ በሩሲያ ላይ ለ10ኛ ጊዜ ማዕቀብ ለመጣል ባደረገው ውይይት ስምምነት ላይ አለመድረሱን ተከትሎ ውሳኔው መራዘሙ ተመላክቷል፡፡

የአውሮፓ ህብረት  ባለፈው ሰኞ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል የወሰነው የፊታችን አርብ የሚከበረውን የሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት አንደኛ ዓመትን አስመልክቶ መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

በማዕቀቡ በአውሮፓ የሚገኙ የሩሲያ ድርጅቶች ሊወጧቸው ይገባል የተባሉ ግዴታዎችን በተመለከተ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሪፖርት ቀርቦ ውሳኔ ይተላለፈበታል ተብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ግጭት ምክንያት በሩሲያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለተጨማሪ አንድ አመት ማራዘሙን አስታውቋል፡፡

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል በሩሲያ ላይ አዳዲስ ማዕቀቦችን ለመጣል በህብረቱ አባል ሀገራት መካከል ክርክሮች መነሳታቸውን ጠቅሰው÷ በቅርቡ ስምምነት ላይ አንደሚደረስ አመላክተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ ሊጥል ያቀደው 10ኛወ ማዕቀብ በሩሲያ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ የከፍተኛ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ሽያጭ የሚከለክል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ክልከላውም 11 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የዋጋ ግምት ያለው መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.