Fana: At a Speed of Life!

የግል ባለሃብቶች በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል ባለሃብቶች በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥሪ አቀረበ።

ባለስልጣኑ የግል ዘርፉ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ላይ ያለውን ተሳትፎ እንዲያጎለብት ባለሃብቶች በተለይም በአነስተኛ የኤርፖርቶች እና ሔሊፖርት ግንባታና አስተዳደር ስራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ አራት ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ደረጃ የተሰጣቸውን ጨምሮ 22 መደበኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ኤርፖርቶች እንዳሉም ተጠቁሟል፡፡

በቁጥርም ይሁን በሚሰጡት የአገልግሎት አድማስና ቅልጥፍና አኳያ በቂ እንዳለሆነም ነው የተመላከተው፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግሥቴ በሰጡት መግለጫ÷ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት መስክ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም መሆኗን አንስተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የአነስተኛ ኤርፖርት እና ሔሊፖርት ግንባታ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማም ክልሎች ሀገራዊ ፋይዳው ከፍተኛ በሆነው ልማት እንዲሳተፉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን÷የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንም ለአልሚዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በፈትያ አብደላ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.