Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ-አቢጃን-ኒው ዮርክ የሚያደርገውን የቀጥታ በረራ በድጋሚ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ-አቢጃን-ኒው ዮርክ የቀጥታ በረራ ከግንቦት 21 ቀን 2015 ጀምሮ በድጋሚ እንደሚጀምር አስታወቀ።

በረራው ከፈርንጆቹ ሰኔ 2019 ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በመጋቢት 2020 መቋረጡን አመልክቷል።

ወደ ኒው ዮርክ የሚደረገው የቀጥታ በረራ በድጋሚ በፈረንጆቹ ጥቅምት 2020 በቶጎ ሎሜ በኩል ተጀምሮ እንደነበር ገልጿል።

በዚህም ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሚጀመረው የአዲስ አበባ- አቢጃን-ኒው ዮርክ የቀጥታ በረራ በሳምንት ለአራት ቀናት እንደሚደረግ አየር መንገዱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው “ የድጋሚ በረራው መጀመር አስደሳች ነው፤ ለመንገደኞችም ተጨማሪ አማራጭ የሚሰጥ ነው” ብለዋል።

በረራው በአሜሪካ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የአየር ትራንስፖርት ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አመልክተዋል።

በተያያዘ ዜና አየር መንገዱ ከግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አሜሪካዋ አትላንታ ከተማ አዲስ የመንገደኞች በረራ እንደሚጀምር ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ130 በላይ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች እና የካርጎ መዳረሻዎች አሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.