Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የእርሻ ትራክተሮችን ለወጣቶች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የእርሻ ትራክተሮችን ለተደራጁ ወጣቶች አስረክቧል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ፥ በካማሽ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ለተደራጁ ወጣቶች ነው የእርሻ ትራክተሮችን ያስረከቡት።

ርዕሰ መስተዳድሩ ትራክተሮችን ለወጣቶች ባሰረኩቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ፥ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ ወጣቶቹ የልማት አጋዥ የሆኑ ትራክተሮችን በመረከባቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት ነው ያሉት አቶ አሻድሊ፥ አሁን የተፈጠረውን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣና የተጎዳውን ኢኮኖሚ ለመጠገን ልማቱ ላይ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

ዞኑ ሰፋፊ ለም መሬት የታደለ ዞን እንደመሆኑ ወጣቶቹ የተሰጣቸውን ትራክተሮች ተጠቅመው ፈጣን ለውጥ እንደሚያመጡም እምነታቸው ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አጥናፉ ባቡር በበኩላቸው የግብርና ስራውን በሜካናይዝድ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በካማሽ ዞን ተዘዋውረው ከህብረተሰቡ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.