Fana: At a Speed of Life!

ከተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ 44 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በንግድ ሥራ ፈቃድ የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን ከተደረገባቸው 500 የንግድ ድርጅቶች ውስጥ ከህግ ውጭ ሲሰሩ በተገኙ 44 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው የንግድ ድርጅቶች በአዋጁ መሰረት የንግድ ስራ ፈቃድ ኖሯቸው ከተፈቀደላቸው መስኮችና ዓላማዎች ውጭ በተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች፣ የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በዘርፉ የተሰማሩ፣ በህግ እና በአስተዳደራዊ እርምጃ የንግድ ሥራ ፈቃዳቸው ተሰርዞ በንግድ ሥራ ላይ የተገኙ የንግድ ተቋማትና የንግድ ፈቃዳቸውን ሳያድሱ ሲሰሩ የተገኙ የንግድ ድርጅቶች መሆናቸውንም አስታውቋል።

በተደረገው የማጣራት ስራ በ26 ድርጅቶች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን በ18ቱ ላይ የፈቃድ ዕገዳ መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.