Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን ልማት ለመደገፍ ዝግጁ ነኝ አለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን ልማት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርዶስ በቀለ ገለጹ።

በቀድሞ አጠራሩ የአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት /ኔፓድ/ በመባል የሚታወቀው አሁን ላይ የአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ የሚባለው የአፍሪካ ሀገራትን የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በመደገፍ የማፋጠን ስራ የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል።

የኤጀንሲው ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርዶስ በቀለ ፥ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ያከናወነች ያለውን የልማት ፕሮጀክቶች ኤጀንሲው ይደግፋል።

በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ያለው የምጣኔ ሃብት እድገት አበረታች መሆኑን ገልጸው ፥ ኤጀንሲው አስፈላጊ በሆኑ ዘርፎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

በጤና፣ በግብርናና በሌሎች አጠቃላይ የልማት ዘርፎች ላይ የሚሰማሩ የግል ባለሃብቶችን ኤጀንሲው ይደግፋልም ነው ያሉት።

በአፍሪካ እንደ አህጉር በጤና፣ በምግብ ዋስትና የመድሃኒት ፋብሪካዎችን በማቋቋምና ሌሎች እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በመጥቀስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

ኤጀንሲው ባደረገው ጥናት መሰረት በአፍሪካ ከሚገኙ 100 ሚሊየን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 92 ሚሊየኑ በኢ-መደበኛ ዘርፍ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም በአፍሪካ እድገት ውስጥ የግሉን ድርሻ ለመጨመር ለእነዚህ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል አቅርቦት፣ የገበያ ትስስር፣ የአቅም ግንባታና ቢዝነስ ፕላን አቀራረጽ ላይ መስራት ይገባል ነው ያሉት።

በ2050 አፍሪካ ይኖራታል ተብሎ ለተተነበየው 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ህዝብ ከወዲሁ የስራ እድሎችን ለማስፋት ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ በአህጉሪቱ የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን በተለይም የአጀንዳ 2063 ትግበራን ለመደገፍ እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ኤጀንሲው የሰው ሃይል አቅም ግንባታ፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የምግብ ዋስትና እንዲሁም ቀጣናዊ ትስስርን ለማሳለጥ የሚሰራ መሆኑ ታውቋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.