Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ም/ቤት የተሻሻሉ አዋጆችንና የዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ጊዜ 2ኛ የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ሶስት የተሻሻሉ አዋጆች፣ የዳኞችና የቋሚ ኮሚቴዎችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

ጉባኤው የክልሉን የ2015 በጀት የግማሽ ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የኦዲት ቢሮ እቅድ አፈፃፀምና በቀጣይ ግማሽ ዓመት የተከለሰ እቅድ ላይ ተወያየቶ በማጽደቅ ነው የተጠናቀቀ፡፡

እንዲሁም የተሻሻለው የክልሉ የኢንቨስትመንት ረቂቅ አዋጅና የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መቋቋሚያ አዋጅን ጨምሮ ሶስት የተሻሻሉ አዋጆችና የ27 ዳኞችና የሶስት ቋሚ ኮሚቴ ሹመትን መርምሮ አጽድቋል።

የምክር ቤቱ ምክትል አፈ- ጉባኤ ወይዘሮ ትሁት ሃዋሪያት አመራሩ ባለፈው ግማሽ በጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስፋትና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዘገብ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በተለይም አመራሩ የኑሮ ውድነት፣ የብልሹ አሰራር፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ የመጠጥ ውሃ ችግሮችን ለማቃለል ከምንጊዜውም በበለጠ በትጋት መስራት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል

ምክር ቤቱ በጉባኤው በስነ-ምግባር ችግር ምክንያት ሁለት የወረዳ ዳኞችን ማሰናበቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክር ቤቱ በመጨረሻም የ27 የወረዳና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመትን ጨምሮ የሶስት ቋሚ ኮሚቴ ሹመት በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል።

ተሿሚዎቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት ህዝቡን በቅንነትና በታማኝነት እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.