Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ገቢዎች ቢሮ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሥድሥት ወራት ከ3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሲዳማ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሃይሉ ጉዱራ እንደገለጹት÷ በግመሽ ዓመቱ ከመደበኛ ግብር ከፋዮች እና መዘጋጃ ቤት አገልግሎት 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነው ወደ ስራ የተገባው፡፡

እቅዱን በተሻለ ሁኔታ ለማሳካትም አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋትና በግብር ከፋዮች ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠር በወቅቱና በታማኝነት እንዲከፍሉ የማድረግ ስራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም ከመደበኛ ግብር ከፋዮች እና መዘጋጃ ቤት አገልግሎት 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን አቶ ሃይሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ገቢው በተለያየ ደረጃ ከሚገኙ 37 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች የተገኘ መሆኑን ነው ሃላፊው የጠቆሙት፡፡

በቀጣይ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉ ቢሮው አስፈላጊውን ቅስቀሳ እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚያከናውን አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም ደረሰኝ የማይከፍሉ ህገ ወጥ ነጋዴዎች በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው አስፈላጊውን ግብር እንዲከፍሉ እና ሀሰተኛ ደረሰኞችን ለመቆጣጠር የተቀናጀ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.