Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን አመራሮች በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን አመራሮች በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርቺሀክ ጋር ምክክር አካሄዱ።

በምክክር መድረኩ ላይ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርቺሀክ እና ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ጄን ማርክ ተገኝተዋል።

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ፣ እስከ አሁን የተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እና ከልማት አጋሮች ጋር በጋራ ስለሚሰሩ ስትራቴጂያዊ የአጋርነትና ትብብር ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሬሚ ከተሰጠው ገለፃ በመነሳት የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የተቋቋመው የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ስራዎች እንዲሳኩ የበኩላቸውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.