Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት በሠላም ተፈቶ ዕርቅ እንዲወርድ ቻይና ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዩክሬን የጦር መሣሪያ መላክ ሠላም አያመጣም ፤ ይልቁንም ሞስኮ እና ኪየቭ ተነጋግረው ችግሮቻቸውን በሠላም ይፍቱ ስትል ቻይና ጠየቀች፡፡

የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አንድ ዓመት መድፈኑን ተከትሎ ተመድ በጠቅላላ ጉባዔው ሀገራቱን የተመለከተ የመፍትሄ ሃሳብ አመላክቷል፡፡

በመፍትሄ ሃሳቡም ሞስኮ ጦርነቱን እንድታቆም እና ወታደሮቿን ከዩክሬን እንድታስወጣ መጠየቁን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ሃሳቡ በ141 ሀገራት ተቀባይነት ሲያገኝ 32 የተመድ አባል ሀገራት ደግሞ ድምፀ-ታዕቅቦ ማድረጋቸው ነው የተጠቆመው፡፡

ሥድስት ሀገራት ከሩሲያ ጎን ቆመው ጉባዔው ያስቀመጠውን የመፍትሄ ሃሳብ ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡

ቻይና ድምፀ-ታዕቅቦ ካደረጉት ሀገራት ተርታ የተሠለፈች ሲሆን ለዩክሬን የጦር መሣሪያዎችን መላክ ጦርነቱን ከማራዘም ውጪ የሚያመጣው ሠላም እንደሌለ ገልጻለች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን የዘለቀው ጦርነት አንደኛ ዓመት መድፈኑን አስመልክቶ ሩሲያን የሚደግፉ ሀገራት ላይ አዲስ ማዕቀቦች እንደሚጣሉ ለማስታወቅ የቡድን 7 አባል ሀገራቱን እና የዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ በሚያካትተው ጉባዔ ላይ በበይነ-መረብ እንደሚካፈሉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.