Fana: At a Speed of Life!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ያለመ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት ያለመ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን በሐረሪ ክልል ተከፈተ፡፡

“ቅርሶቻችን ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ልማት” በሚል መሪ ሐሳብ የተከፈተውን ኤግዚቢሽን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እና የሐረሪ ክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ናቸው፡፡

የሐረሪ ክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተወለዳ አብዶሽ ኤግዚቢሽኑ በሀገሪቱ ያሉትን ቅርሶች ከማስተዋወቅና ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡ በሀገሪቱ የሚገኙ ቅርሶችን በተጨባጭ እንዲገነዘብ ማስቻልና በክልሉ የሚገኙ ቅርሶች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግ የኤግዚቢሽኑ ዓላማ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የጎብኚ ፍሰትን ለማሳደግና የሀገር ውስጥ ጎብኚን ለመጨመር የኤግዚቢሽኑ ሚና የጎላ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም ዋና ዳይሬክተር ደምረው ዳኜ እንደገለጹት÷ ከማህበረሰቡ ባለፈ በዋናነት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚያገኟቸው እውቀት ባሻገር በተግባር የሚያገኟቸውን ክህሎት ለማዳበር ኤግዝቢሽኑ ያግዛል፡፡

ለተከታታይ አምስት ቀናት ክፍት ሆኖ በሚቆየው ኤግዚቢሽን÷ ሉሲ (ድንቅነሽን) ጨምሮ ሌሎች ቅርሶች ለእይታ ቀርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.