Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የከተማ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎችን ውጤታማ የሚያደርጉ አሰራሮች እየተከተሉ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎችን በተሻለ ውጤታማ የሚያደርጉ አሰራሮች እየተከተሉ መሆኑን የኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ገለፁ፡፡

ከዚህ ቀደም እንደ ችግር በክልሎቹ ይስተዋሉ የነበሩትን የውሃ ፣የመብራት እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተናቦ የመስራት ችግርን ለመፍታት በተሰራው ስራ የተሻለ የመሰረተ ልማት ግንባታ ውጤት እያሳዩ መሆኑንም አንስተዋል።

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የረጂ አካላት ድጋፍና ብድርን መሰረት በማድረግ 17 ከተሞች በመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አንስቷል።

በረጂ አካላት ተደራሽ ያልሆኑ ከተሞችንም ተጠቃሚ ለማድረግ በዚህ አመት ብቻ ከ150 ሚሊየን ብር በላይ የክልሉ መንግስት ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ አፈወርቅ ለማ ተናግረዋል።

እንደ ኦሮሚያ ክልልም የመብራት፣ውሃ እና የመንገድ የመስመር ዝርጋታ ላይ የነበረን ቅንጅታዊ የአሰራር ክፍተት ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ክልሉ አስታውቋል።

በዚህም ፕሮጀክቶቹ ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በቅንጅት ሊያሰሩ የሚችሉ መንገዶችን መከተልን በማስቀደም እየተሰራ ነው ሲሉ የክልሉ የከተማ ክላስተር ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ገ/ህይወት ገልጸዋል።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.