8ኛው የአፍሪካ ተማሪዎች ምገባ ቀን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ይከበራል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)8ኛው የአፍሪካ የተማሪዎች ምገባ ቀን አዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚከበር ተገለጸ፡፡
ቀኑን በማስመልከት ” የምግብ ግዥ ሥርዓቶችን እና የዕሴት ሰንሰለቶችን ማሳደግ የአፍሪካውያን አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሚና ለዘላቂ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞች እና ለተሻሻለ ትምህርት” በሚሉ መሪ ቃሎች በበይነ-መረብ ውይይት ይካሄዳል።
ውይይቱ በፈረንጆቹ የፊታችን የካቲት 27 እንደሚጀመርና እስከ መጋቢት 1 ቀን 2023 እንደሚቆይ ከአፍሪካ ኅብረት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
መርሃ ግብሩ በአዲስ አበባ አፍሪካ ኅብረት አዳራሽ እና በሞሮኮ ማራካሽ ይካሄዳል ነው የተባለው፡፡
በመድረኩ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ÷ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ የትምህርት፣ ሣይንስ ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ኮሚሽነር የሆኑት አልጄሪያዊው ፕሮፌሰር ሞሐመድ ቤልሆሲን ፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ ÷ እንዲሁም የሌሎች የተመድ ኤጀንሲዎች ተወካዮች ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።