Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከኢስት አፍሪካ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከኢስት አፍሪካ ኢንደስትሪያል ፓርክ ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ከሚሽኑ በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ስምምነቱ ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ኩባንያን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክነት ለማሳደግ የሚያስችል የአልሚነት ስምምነት ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በ100 ነጥብ 6 ሄክታር ላይ የሚለማው ኢስት አፍሪካ ኢንዱትሪያል ፓርክ የተለያዩ የአምራች ኢንደስትሪዎችን በማካተት እየሰራ እንደሚገኝ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ተመላክቷል፡፡

ፓርኩ የስራ ዕድልን በመፍጠር፣ የክህሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግርን በማጎልበት እዲሁም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ ረገድ የራሱን ጉልህ ድርሻ እንደሚወጣም ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.