Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ 200 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የዘላቂ ማረፊያዎችን ደረጃ የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ከ199 ነጥብ 582 ሺህ ብር በላይ ወጪ የሦስት ዘላቂ ማረፊያዎችን ደረጃ ለማሳደግ የግንባታ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ፡፡

የደረጃ ማሳደግ ግንባታው እየተከናወነ ያለው÷ በጀሞ፣ ጉራራ እና ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ዘላቂ ማረፊያዎች መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሠረት ለጀሞ ዘላቂማረፊያ 118 ሚሊየን 237 ሺህ 437 ብር ፣ ለጉራራ 41 ሚሊየን 627 ሺህ 284 ብር እና ለጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ዘላቂ ማረፊያ 39 ሚሊየን 717 ሺህ 428 ብር በላይ ተመድቦ ግንባታቸው እየተከናወነ ነው፡፡

ዘላቂ ማረፊያዎቹ ከቀብር አገልግሎት ባሻገር የመታሰቢያ ፓርክ፣ ውብ እና አማራጭ የመዝናኛ ቦታ እንዲሆኑ ታስቦ ነው የግንባታ ሥራዎቹ እየተከናወኑ ያሉት፡፡

በቢሮው የተቀናጀ ዘላቂ ማረፊያ ዳይሬክተር አጃኢብ ኩምሳ ግንባታውን እስከ 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ለማጠናቀቅ መታሰቡን እና እነዚህ ሲጠናቀቁ ሌሎቹን የመገንባት ሥራ ይጀመራል ብለዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ቢሮው ከያዘው ራዕይ ጋር የዘላቂ ማረፊያዎችን ቦታ ደረጃቸውን ማስጠበቅና የአረንጓዴ ማዕከል የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በመንግሥት የሚተዳደሩ 15 እንዲሁም በእምነት ተቋማት የሚተዳደሩ 75 ዘላቂ ማረፊያዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.