Fana: At a Speed of Life!

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጄክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዚየም ፕሮጀክትን ጎበኙ፡፡

የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጄክት በ3 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ እና ባለ አምስት ወለሉ ፕሮጀክት የአድዋን ድል፣ የኢትዮጵያውያንን ጀግኖች፣ የአድዋን መልክዓምድር በሚወክል መልኩ እየተገነባ ይገኛል።

ሙዚየሙ በአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር መነሻ የተሰየመው የአንድነት መነሻ ማዕከል ተደርጎ በመቆጠሩ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን በጥቅምት 2016 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙዚየሙ የአድዋን ሰንሰለታማ ተራሮች፣ የፈረሰኞች ፣ ለሴት ጀግኖች ክብር የተሰየመ ማስታወሻ፣ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነፃነት ማስታወሻ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖች ጉዞና 5 የመግቢያ በሮች እንዳሉት ተመላክቷል።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ምክርቤት አዳራሽን ጭምሮ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ አዳራሽ 1 ሺህ መኪኖችን የሚያስተናግድ የመኪና ማቆሚያ እና መዝናኛ ስፍራዎች እንዳሉት ኢዜአ ዘግቧል፡፡7

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.