Fana: At a Speed of Life!

የጀግኖችን ቅርስ በማሰባሰብ ትውልድ እንዲማርበት ይደረጋል- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ያለፉትን እና አሁን ያሉትን ጀግኖች የጀግንነት ማሳያ ቅርስ በማሰባሰብ ትውልዱ እንዲማርበት ይደረጋል አሉ፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እና ከፍተኛ አመራሮች የመከላከያ ወታደራዊ ቅርስ ጥበቃ እና ሙዚየም ዳይሬክቶሬትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ባደረጉት ንግግር÷ የዘንድሮውን የዓድዋ ድል በዓል በመሪነት የሚያከብረው መከላከያ ስለሆነ ዳይሬክቶሬቱ በባለቤትነት ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል፡፡
ወታደራዊ ቅርሶች ተለይተውና ጥናት ተደርጎባቸው ለሀገር እንዲጠቅሙ እየተሠራ መሆኑን የመከላከያ ወታደራዊ ቅርስ ጥበቃ እና ሙዚየም ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱልቃድር ደባሹ ተናግረዋል፡፡
ከ500 በላይ ወታደራዊ ቅርሶች፣ ማህተሞች እና ቲተሮችን ጨምሮ ሌሎች ቅርሶችን ማሰባሰብ ተችሏል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.