Fana: At a Speed of Life!

በወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በሐረሪ ክልል የተለያዩ ስፍራዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በሐረሪ ክልል የተለያዩ ስፍራዎችን ጎበኘ፡፡

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልኡክ በሐረር ጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የተመለከቱ ሲሆን የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችንም ጎብኝተዋል።

የልዑካን ቡድኑ በተለይም በሐረር ጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ የተከናወኑ የአረንጓዴ ልማትና የመንገድ ዳር መብራት ስራዎችን ነው ተዘዋውረው የተመለከቱት።

ልዑካን ቡድኑ በጁገል ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን አድንቀው በቀጣይም መሰል የልማት ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም መጠቆማቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም ሐረር ከተማ ከሚገኙ የቱሪስት መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን የጅብ ማብላት ትርኢት ላይም ታድመዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሄለን ደበበ እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.