Fana: At a Speed of Life!

አማራ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት የኢንቨስትመንት ንቅናቄ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ  አቶ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በኢንቨስትመንት ካደጉ ሀገራት ተሞክሮ ተወስዶ የተጀመረ ነው ብለዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ንቅናቄው ለአሥርት ዓመታት እንዲቆይ ታቅዶ የተጀመረ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ  ሕዝቡን ተወዳደሪና ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ የተጀመረ ንቅናቄ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በአማራ ክልል በጦርነት ወድመው  የነበሩ ኢንዱስትሪዎችን መልሶ ለመገንባት እቅድ ተይዞ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ባለፉት ጊዜያት በተደረጉ ንቅናቄዎችም የአማራ ክልል ሰፊ አቅም ያለውና ከፍተኛ የሆነ ምርት ማምረት እንደሚችል ያሳየበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመድረኩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች  እና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች መገኘታቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.