Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶቿ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥረት እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶቿ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ አስፈላጊውን ጥረት እንደምታደርግ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ተናገሩ፡፡

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ዩን ሶክ ዮል ልዩ መልዕክተኛ ጃንግ ሱንግ ሚን እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ በግድ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ሀገራቱ በተይም በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ መንግስት የሀገሪቱ ተጨማሪ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ፍላጎት እንዳለውም አረጋግጠዋል፡፡

ለዚህም ባለሃብቶቹ ቢሰማሩ ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት የሥራ ሃላፊዎች ጋር ምክክር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

ባለሃብቶቹ በጤና፣ በትራንስፖር እና በማምረቻው ዘርፍ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እና በኢትዮጵያ ያለውን እምቅ ሃብት በተመለከተ መረጃ እንደሚሰጣቸውም አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙም ነው የተናገሩት።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.