Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለህክምና ባለሙያዎች ልብስ መግዣ የሚሆን የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ።

የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ለህክምና ባለሙያዎች ልብስ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ለመግዛት የገንዘብ ድጋፉ መደረጉን ገልጸዋል።

ሀኪሞች የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በቀጥታ ከህሙማን እና ተጠርጣሪዎች ጋር የሚገናኙ እና ለህሙማን ምግብ የሚያቀርቡ እንደመሆናቸው ቅድሚያ ለእነርሱ በመስጠት ቁሳቀሱን ማሟላት ማስፈለጉን ነው የገለፁት።

ምክር ቤቱ ከክልል እስከ ቀበሌዎች ባለው መዋቅር ህብረተሠቡ ከኮሮና ቫይርስ ራሱን እንዲጠብቅ በተዳራጀና በተቀናጀ አግባብ የግንዛቤ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን አፈጉባዔው አንስተዋል።

በቀጣይም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ምክር ቤቱ አሁን የጀመረውን ስራ በቅንጅት ከማህበረሰቡ ጋር አጠናክሮ ይሰራል ብለዋል።

በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕርግ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሙልነሽ አበበ ድጋፉን ከአፈጉባኤ ወርቅሰው ማሞ ተረክበዋል።

ችግር እየሆነ ያለው የጤና ባለሙያዎች የመከላከያ ጋዎንና ጭንብል እንደሆነ በማንሳት ምክር ቤቱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

በተጨማሪም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቫይረሱን በመከላከሉ ከፊት ሆነው እየሰሩ ላሉት ሀኪሞች መከላከያ የሚሆን ጋውንና ጭንብል ማምረት በመቻሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

 

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.